ዶ/ር መረራ ጉዲና የታሠሩት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ክልከላ በመተላለፋቸው መሆኑን የገለፁት የመንግሥቱ ቃል አቀባይ ተጨማሪ መረጃ በሂደት ሊገኝ የቻለው ከሕግ አካላት ወይንም ከማዘዣ ጣቢያው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባ —
“ኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን እያሰረች ነው” የሚለው አባባልም ያለውን ሁኔታ አያንፀባርቅም ሲሉ ተችተዋል፡፡
ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ለሚገኙ የውጭ ሀገር የዜና ወኪሎች መግለጫ የሱጡ ሲሆን፣ በመግለጫቸው ከሁለት ቀናት በፊት የታሠሩት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ መስራችና ሊቀመንበር እንደዚሁም የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ማብራሪያ አልሠጡም፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
የኢትዮጵያ መንግሥት የዶ/ር መረራ እስር ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር የተገናኘ ነው አለ