የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነጮቹ ገበሬዎች መሬታቸውን እየተቀሙ ይገደላሉ ብለው በትዊተር መፃፋቸው ተከትሎ የዘር ክፍፍል እየቀሰቀሱ ናቸው ስትል ደቡብ አፍሪካ ወነጀለቻቸው።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በዋይት ኃውስ ኦፊሴላዊ ትዊተራቸው ባለፈው ማከሰኞ ባወጡት ቃል ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሚካሄደውን የመሬት ነጠቃ እና በስፋት የሚፈፀመውን ግድያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዎ በቅርበት ይከታተሉ ሲል ጠይቀዋል።
I have asked Secretary of State @SecPompeo to closely study the South Africa land and farm seizures and expropriations and the large scale killing of farmers. “South African Government is now seizing land from white farmers.” @TuckerCarlson @FoxNews
— Donald J. Trump (@realDonaldTrump) August 23, 2018
ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ያወጡትን አዲስ የመሬት ይዞታ ለውጥ ዕቅድ ተከትሎ ነው።
የደቡብ አፍሪካ መንግሥት በሰጠው ምላሽ የሚስተር ትረምፕን ቃል አገራችንን ለመከፋፈል እና ያለፈውን የቅኝ አገዛዝ ዘመን ለማስታወስ የየታለመ ጠባብ አመለካከት ፈፁሞ አንቀበልም ብሉዋል። አስከትሎም ደቡብ አፍሪካ የመሬት ይዞታ ለውጥ ርምጃዎቹዋን ሃገረችንን በማይከፋፍልመንገድ በጥንቃቄ ታካሂዳለች ሲል አስታውቁዋል።