ዩናይትድ ስቴትስ በሶማሊያ የዘጋችውን የዕርዳታ ቋሚ ሚሽን ልትከፍት ነው

  • ቪኦኤ ዜና
ዩናይትድ ስቴትስ በሶማሊያ ከሃያ ስምንት ዓመታት በፊት የዘጋችውን የዓለምቀፍ ልማት ዕርዳታ ቋሚ ሚሽን ልትከፍት ነው።

የዩኤስኤይድ እኤአ ከጥር አምስት 1991 ጀምሮ ተዘግቶ ቆይቷል።

ዩናይትድ ስቴትስ ከሶማሊያ ጋር ግንኙነቷን በይፋ ያላቋረጠች ቢሆንም በዚያች ሃገር እ ኤ አ በ1980ዎቹ ጀምሮ የተካሄደው የርስ በርስ ጦርነት በ ዘጠና አንድ ማዕከላዊ መንግሥቱ ማንኮታኮቱን ተከትሎ ኤምባሲዋን መዝጋቷ ይታወሳል።

ለሶማሊያ ህዝብ ሰብዓዊ ዕርዳታ የሚውል ወደ አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ዕርዳታ መመደቡን ዩ ኤስ ኤድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ሞቃዲሾ ውስጥ የዩ ኤስ ኤድ ሚሽን መከፈቱ ዩናይትድ ስቴትስ ከሶማሊያ ህዝብ ጋር ያላትን የልማት አጋርነት የሚያጠናክር ታላቅ ምዕራፍ ነው ብሏል መግለጫው።