ማንቢጅ በተባለች የሰሜን ሶርያ ከተማ በሚገኝ ምግብ ቤት ውጭ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ራሱን በማፈንዳቱ አራት አሜሪካውያን ተገድለዋል። አሜሪካውያን ሙሉ በሙሉ ከሶርያ ሲወጡ ምን ሊሆን እንደሚችል ጥያቄ አስነስቷል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ማንቢጅ በተባለች የሰሜን ሶርያ ከተማ በሚገኝ ምግብ ቤት ውጭ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ራሱን በማፈንዳቱ አራት አሜሪካውያን ተገድለዋል። አሜሪካውያን ሙሉ በሙሉ ከሶርያ ሲወጡ ምን ሊሆን እንደሚችል ጥያቄ አስነስቷል።
“እስላማዊ መንግሥት ነኝ” የሚለው አሸባሪ ቡድን ትናንት ለተፈፀመው ጥቃት በፍጥነት ኃላፊነቱን ወስዷል። አጥፍቶ ጠፊው ከሶርያውያን ተውጊዎቹ አነዱ ነው ካለ በኋላ የዩናይትድ ስቴትስና የጥምረት ኃይሎች የጥበቃ ክፍልን ዒላማ እንዳደረገ ገልጿል።
በከተማይቱ የሚገኙ ሀኪሞች ሁለት አሜሪካውያን ወታደሮች ወድያውኑ መገደላቸውን ተናግረዋል። የቆሰሉት ግን በፍጥነት ወደ ጎረቤት ሃገር ኢራቅ ለህክምና እንደተወሰዱ በዩናይትድ ስቴትስ የሚደገፈው የሶርያ ዲሞክራስያዊ ኃይሎች ኃላፊዎች ጠቁመዋል።
የአሜሪካ ወታዳራዊ ኃይል ባወጣው መግለጫ አንድ ሲቪል ሰራተኛና በመከላከያው ክፍል በኮንትራት የሚሰራ ሰው በፍንዳታው እንደተገደሉ ትላንይ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።