የዩናይትድ ስቴትስ ወግ አጥባቂ ቡድኖች ታዋቂ ሰዎች በማኅበራዊ መገናኛ ስለሚሰራጩ ዘገባዎች ለመወያየት ዛሬ ዋይት ኃውስ ውስጥ ይታደማሉ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ግዙፎቹ የማኅበራዊ መገናኛ ድርጅቶች ትዊተርና ፌስቡክ ግን በጉባዔው አይሳተፉም፣ እንደዘገባዎች ከሆነ አልተጋበዙም።
ስለዋይት ኃውሱ ጉባዔ እና ስለተሳታፊዎቹ ብዙ የሚሰማ ዝርዝር የለም። ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት አንዳንዶች እነዚህን ኩባኒያዎች ወግ አጣባቂ ድምፆችን ያፍናሉ ብለው በስፋት ይወነጅላሉ። ሊሎች ደግሞ የማኅበራዊ መገናኛ ኩባኒያዎቹ ተጠቃሚውን ከሃሰት መረጃና ስርዓት ከጎደላቸውና ጠብ ከሚጭሩ መልዕክቶች ለመጥበቅ በቂ ዕርምጃ አልወሰዱም ሲሉ ይወቅሷቸዋል፡፡
አንዱ የማያከራክረው ዕውነት ታዲያ የቴክኖሎጂ ኩባኒያዎቹ የመረጃና የንግድ ልውውጡን እንቅስቃሴ ከፍተኛ የሆነ ጉልበት ያላቸው መሆኑ ነው።