የዩናይትድ ስቴትት መንግሥት ባጋጠመው የፖለቲካ መፋጠጥና በዚህ ዘመን በጀት መንጠፍ ምክንያት ለ35 ቀናት ከተዘጋ በኋላ በወዲያኛው ዓርብ ምሽት ተከፍቷል።
ለመሆኑ የዚህ መንግሥት የመዝጋት አባዜ ለዩናይትድ ስቴትስ ምንድነው? ለምን የዩናይትድ ስቴትስ ፈሊጥስ ሆነ? ጥቅምና ጉዳት ይኖረው ይሆን?
የመዘጋቱ ዳራ፣ ይዘትና መዘዝ ...
በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና በተወካዮች ምክር ቤቱ አፈጉባዔ ናንሲ ፔለሲ መካከል የተፈጠረው መፋጠጥ ለውጥ አላሳየም። ፕሬዚዳንቱ ዩናይትድ ሰቴትስ ከሜክሲኮ ጋር በምትዋሰንበት የደቡብ ድንበር ላይ ‘አቆመዋለሁ’ ሲሉ ከ‘ምረጡኝ’ ዘመቻቸው ወቅት አንስቶ ይዘውት የነበረውን የግንብ ወይም የአጥር አቋማቸውን አጠናክረውና አምርረው ቀጥለውበታል። አፈጉባዔዋና ዴሞክራቲክ እንደራሴዎቹ ደግሞ ይህንን የአጥር ነገር መስማት አይፈልጉም። መንግሥቱ ከወር በላይ የተዘጋው በዚሁ ሰበብ ነው። እንደገና ላለመዘጋቱ ዋስትና የለም።
“ከፕሬዚዳንቱ ዛቻና ፉከራ በመነሣት ቢዘጋ አይደንቀኝም” ይላሉ የኦሃዮ ዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሣይንስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ብሩክ ኃይሉ።
ዘገባውንና ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉን ትንታኔ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5