በአሜሪካዊያን ሴቶች ለዘመናት በዝምታ ያለፏቸውን የፆታ ትንኮሳዎች፣ ጉንተላዎችና አስገድዶ መደፈር ታሪኮች በይፋ እየተናገሩ፤ በተለይ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ታዋቂ ሰዎች ፈጸሟቸው የተባሉት የህዝብ መነጋገሪያ ሆኗል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በዩናይትድ ስቴይትስ ታዋቂ ሰዎች ላይ እየተሰሙ የሚገኙ የወሲባዊ ጥቃት ውንጀላዎች አሁን ወደ ሜኔሶታው ዴሞክራቲክ ሴናተር አል ፍራንኪን አነጣጥሯል።
ከ11ዓመት በፊት በመካከለኛው ምሥራቅ ለዩናይትድ ስቴይትስ ጦር በተዘጋጁ የመዝናኛ ዝግጅቶች ላይ አንዲት የራድዮ ጋዜጠኛን ያለፍላጎቷ ከንፈር ስመዋል፣ ጎንትለዋል በሚል ተወንጅለዋል።
Your browser doesn’t support HTML5
ሊድያ ትዊድን አል ፍራንክን በፃፉት የቀልድ ድርሰትን ለማቅረብ ሲዘጋጁ፤ ያለፍላጎቷ መሳሟንና መጎንተሏን ተናግራለች። የሪፖብሊካን ፓርቲው የአላባማ ሴኔት ዕጩ ተወዳዳሪም ዕድሜያቸው ለአቅመ ሔዋን ያልደረሱ ልጃገረዶች ላይ የወሲብ ጥቃት ፈፅመዋል በሚል ውንጀላ ቀርቦባቸዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5