በአሜሪካ ዓውሎ ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ 18 ሰዎችን ገደለ

ዓውሎ ነፋሱ መኖሪያ ቤቶችን እና የከባድ መኪና ሾፌሮችን መጠለያ እንዲሁም የተንቀሳቃሽ ቤቶችን ፓርክ  አውድሟል።

ዓውሎ ነፋሱ መኖሪያ ቤቶችን እና የከባድ መኪና ሾፌሮችን መጠለያ እንዲሁም የተንቀሳቃሽ ቤቶችን ፓርክ  አውድሟል።

በቴክሳስ፣ ኦክላሆማ እና አርካንሳ በጣለው ዓውሎ ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ 18 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

ዓውሎ ነፋሱ መኖሪያ ቤቶችን እና የከባድ መኪና ሾፌሮችን መጠለያ እንዲሁም የተንቀሳቃሽ ቤቶችን ፓርክ አውድሟል።

በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶች ካለ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባቸዋል።

ማዕበሉ ዛሬ ሰኞ ወደ ምሥራቅ የሃገሪቱ ክፍል በማምራት ከአላባማ እስከ ኒው ዮርክ ያሉ ግዛቶችን እንደሚመታ የአየር ትንበያ ባለሙያዎች በመናገር ላይ ናቸው።

በኬንተኪ አገር ገዢው ዛሬ ማለዳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል። አውሎ ነፋሱ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንም አስተውቀዋል።

በቴክሳስ ግዛት 100 የሚሆኑ ሰዎች ላይ ጉዳት ሲደርስ ከ200 በላይ መኖሪያ ቤቶችና ሌሎችም ሕንጻዎች ወድመዋል።