ተመድ በሮሒንግያ ሙስሊሞች ስደት አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው

  • ቪኦኤ ዜና
ምዕራባዊ ሚያንማር ውስጥ በተቀሰቀሰውና ወደ 4መቶ ሺህ የበሮሒንግያ ሙስሊሞች፣ ድንበር አቋርጠው ወደ ባንግላዴሽ እንዲሰደዱ ያስገደደውን ቀውስ በተመለከተ፣ የተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት በዚህ ሳምንት ውስጥ አንድ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያካሂድ ተገለጸ።

ምዕራባዊ ሚያንማር ውስጥ በተቀሰቀሰውና ወደ 4መቶ ሺህ የበሮሒንግያሙስሊሞች፣ ድንበር አቋርጠው ወደ ባንግላዴሽ እንዲሰደዱ ያስገደደውን ቀውስ በተመለከተ፣ የተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት በዚህ ሳምንት ውስጥ አንድ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያካሂድ ተገለጸ።

ለነገ ረቡዕ የተቀጠረው የምክር ቤቱ ስብሰባ እንዲጠራ የተጠየቀው በብሪታንያና በስዊድን ሲሆን፣ ይህም የተመድ የሰብዓዊ አገልግሎት ዋና ኃላፊ ዘይድ ራአድ አል ሁሴን ትናንት ሰኞ፣ ድርጊቱ የዘር ማፅዳት ምሳሌ መሆኑን ከገለፁ በኋላ ነው።

Your browser doesn’t support HTML5

ተመድ በሮሒንግያ ሙስሊሞች ስደት አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂድ ነው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ሃላፊ ዘይድ ረአድ አል ሁሴን መንግሥታት ወደ አምባገንንነትና ወደ ጭቆና እንዲሁም ሰብዓዊ መብትን ወደ መርገጥ እያመሩ ናቸው ሲሉ ነበር ትናንት ያስጠነቀቁት።

የተመድ የሥደተኞች መሥራያ ቤት፣ አመፁ ከተቀሰቀሰበት ካለፈው ከነሐሴ 19 ወዲህ፣ ወደ 370,000 የሮሒንግያ ነዋሪዎች ወደ ባንግላዴሽ እንደተሰደዱ አመልክቶ፣ በተያያዘ ግጭትም 400 ያህል ሰዎች እንደሞቱ ገልጧል።