የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል ሶማልያ ውሰጥ ሥልሳ አማጽያን እንደተገደሉ ገለፀ

  • ቪኦኤ ዜና
የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል ሶማልያ ውሰጥ በአል ሸባብ ላይ በአካሄደው የአየር ድብዳባ 60 አማጽያን እንደተገደሉ ገልጿል። ለአንድ ዓመት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ ባልታየ መልኩ ብዙ አማጽያን የተገደሉበት ተድርጎ ታይቷል።

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል ሶማልያ ውሰጥ በአል ሸባብ ላይ በአካሄደው የአየር ድብዳባ 60 አማጽያን እንደተገደሉ ገልጿል። ለአንድ ዓመት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ ባልታየ መልኩ ብዙ አማጽያን የተገደሉበት ተድርጎ ታይቷል።

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ እዝ ባለፈው አርብ በሚዱግ ክፍለ-ሀገር ባለው ሃራርዴሬ የሶማልያ ማኅበረስብ አጠገብ ላይ የአየር ድብደባ ማካሄዱን አስታውቆ ነበር።

ዛሬ የወጣው መግለጫ በወታደራዊው ግምገማ መሰረት የተገደለ ወይም የቆሰለ ሲቪል የለም ይላል። ስለደረሰው ጉዳትም ሆነ ሞት በነፃ ምንጭ አልተረጋገጠም።

ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ላይ በተካሄደ የአሜሪካ የአየር ድብደባ በ100 የሚገመቱ የአል ሸባብ አማፅያን ተግደዋል።