ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰለ ሩሲያ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቅርብ ተባባሪዎቻቸውና የምርጫው ጊዜ አማካሪዎቻቸው ከሩስያ ቅርብ ግንኙነት ነበራቸው የሚለውን ወሬ አልተቀበሉም።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቅርብ ተባባሪዎቻቸውና የምርጫው ጊዜ አማካሪዎቻቸው ከሩስያ ጋር ቅርብ ግንኙነት ነበራቸው የሚለውን ወሬ አልተቀበሉም። ከብሔራዊ ፀጥታ አማካሪነት ስልጣናቸው ለመውረድ ለተገደዱት ማይክል ፍሊን ትላንት ተከላክለዋል።

ፍሊን ከሩስያ ባለስልጣኖች ጋር ያላቸውን ግንኙነት አስመልክቶ ለተፈጠረው ጭቅጭቅ ትራምፕ ተጠያቂ ያደረጉት ጥቅስ “ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ የመረጃ ሾልኮ መውጣት” ያሉትን ነው።

በጉዳዩ ላይ ነፃ ምርመራ ቢደረግ የትራምፕ አስተዳደር ችግር ላይ ይወድቃል ሲሉ አንድ ተንታኝ መናገራቸውን የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ዘጋቢ ላቲካ ሆክ ባጣናቀረችው ዘገባ ጠቅሳለች።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰለ ሩሲያ