የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች - ሰለ ዶናልድ ትራምፕ

  • እስክንድር ፍሬው

ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ

ልክ የዛሬ ሣምንት ዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በመሆን ቃለ መሓላ ይፈጽማሉ። አዲሱ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ላይ የሚከተሉት ፖሊስ ከተሰናባቹ ፕሬዚዳንት አንድ ሊሆን እንደሚችል የቀድሞ የፓርላማ አባላትና የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ይናገራሉ።

ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ የተለየ ነገር እንዳልሰሩ የተናገሩት የቀድሞ የፓርላማ አባልና የፓን አፍሪካን ፓርላማ የክብር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ “ከሳቸው የከፋ ይመጣል ብዬ አላስብም”ብለዋል።

ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ጠንካር ግንኙነት መኖሩን ያስታወሰው የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ይኸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነቱን ገልጿል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች - ሰለ ዶናልድ ትራምፕ