የዓለም መሪዎች ለዶናልድ ትረምፕ የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት እያስተላለፉ ነው

  • ቪኦኤ ዜና

የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ

ትላንት ማክሰኞ በዩናይትድ ስቴትስ በተካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትረምፕ ወሳኝ ድል ማግኘታቸው የሚያመለክቱ ትንበያዎች በዜና ማሰራጫዎች መውጣት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የዓለም መሪዎች የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት አስተላልፍውላቸዋል፡፡

በምርጫው የዲሞክራቲክ ፓርቲው ተቀናቃኛቸው ምክትል ፕሬዚደንት ካምላ ሀሪስን ያሸነፉት ሪፐብሊካኑ የቀድሞ ፕሬዝደንት ትረምፕ ከአራት ዓመታት በኋላ ወደ ኋይት ሃውስ በመመለስ ታሪክ አስመዝግበዋል፡፡

ዛሬ ረቡዕ ማለዳ በርካታ የዓለም መሪዎች 47ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ኾነው በድጋሚ ለተመረጡት ትረምፕ በኤክስ ማኅበራዊ መገናኛ የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት ልከውላቸዋል፡፡

ዶናልድ ትረምፕ በመጀመሪያው የአስተዳደር ዘመናቸው "ቅድሚያ ለአሜሪካ" በሚል የተከተሉት የውጭ ፖሊሲ አቅጣጫቸው ዩናይትድ ስቴትስ ከበርካታ አጋሮቿና ባላንጣዎቿም ጋራ ያላትን ግንኙነት አወሳስቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ለአዲስ ተመራጩ ፕሬዝደንት ቀድመው መልዕክት ከላኩት የዩናይትድ ስቴትስ አጋሮች መካከል አንዱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ናቸው፡፡ "ወደመሪነት በድጋሚ በመመለስ ታሪክ ሠርተዋል " በማለት ያደነቁት ኔታንያሁ የእስራኤል እና የአሜሪካን ታላቅ አጋርነት ይበልጡን የሚያጸናው እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

የሩስያን ጥቃት ለመመከት ዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎችም ምዕራባዊያን አጋሮች ተጨማሪ ድጋፍ እንዲሰጡ የሚማጸኑት የዩክሬይን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ በበኩላቸው በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ትረምፕ የሚከተሉት "ሰላም በጥንካሬ" ቁርጠኛ አቋም ያሉትን አስመልክተው አዎንታዊ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

“ዩክሬይንን ተገቢውን ሰላሟን የምታገኝበት ቀን እንዲቀርብ ሊያደርግ የሚችለው ይህ መርህ ነው “ ያሉት ዜሌንስኪ “አብረን ተግባር ላይ እንደምናውለው ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል፡፡

የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ ዋና ጸሐፊ ማርክ ሩተ ተመሳሳይ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑዌል ማክሮንም ፈጥነው የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን እንደፊተኞቹ አራት ዓመታት አሁንም በሁለታችንም ቁርጠኝነት አብረን ለመሥራት ዝግጁ ነኝ ብለዋል፡፡

የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ኪር ስታርመር በበኩላቸው መንግሥታቸው የጋራ የሆኑትን የነጻነት የዲሞክራሲ እሴቶቻችንን ለመከላከል አብሮ እንደሚቆም ተናግረዋል፡፡ የሩሲያ ፕሬዝደንት ቪላዲሚር ፑቲን በምርጫው ውጤት ላይ አሰተያያት አልሰጡም፡፡ የቀድሞው የሩስያ ፕሬዚደነት ዲሚትሪ ሜድቬዲየቭ ግን በኤክስ ገጻቸው ካማላ ሃሪስ በመሸነፋቸው ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ ዋና ጸሐፊ ማርክ ሩተ ተመሳሳይ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኢማኑዌል ማክሮንም ፈጥነው የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን እንደፊተኞቹ አራት ዓመታትአ ሁንም በሁለታችንም ቁርጠኝነት አብረን ለመስራት ዝግጁ ነኝ ብለዋል፡፡

የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ኪር ስታርመር በበኩላቸው መንግሥታቸው የጋራ የሆኑትን የነጻነት የዲሞክራሲ እሴቶቻችንን ለመከላከል አብሮ እንደሚቆም ተናግረዋል፡፡

የሩሲያ ፕሬዚደንት ቪላዲሚር ፑቲን በምርጫው ውጤት ላይ አሰተያያት አልሰጡም፡፡ የቀድሞው የሩስያ ፕሬዚደነት ዲሚትሪ ሜድቬዲየቭ ግን በኤክስ ገጻቸው ካማላ ሃሪስ በመሸነፋቸው "አለቀላቸው" በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

የእስያ መሪዎችም የደስታ መግለጫ መላካቸውን ቀጥለዋል፡፡ የህንድ ጠቅላይ ሚንስትር ኔራንድራ ሞዲ “ጓደኛዬ” ሲሉ ለጠሯቸው ለዶናልድ ትረምፕ "እጅግ ከልቤ እንኳን ደስ ያለዎ" እላለሁ የሚል መልዕክት ሰድደውላቸዋል፡፡ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚደንት ዩን ሱክ ዬዎል፡ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺጌሩ ኢሺባ እና የፊሊፒንስ ፕሬዝደንት ፈርዲናንድ ማርኮስ እንዲሁም የአውስትሬሊያ ጠቅላይ ሚንስትር አንተኒ አልባኔዝ የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ በበኩላቸው ቤጂንግ የቻይና እና የዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነቶችን በጋራ መከባበር በሰላም አብሮበመኖር እና በጋራ ጥቅም ላይ በተመሰረት ትብብር መርሃችን ማስተናገዷን ትቀጥላለች" ብለዋል፡፡