በዋሽንግተን ዲሲው የዓየር ላይ ግጭት አደጋ በሕይወት የተረፈ ሰው እንዳልተገኘ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በዋሽንግተን ዲሲው የዓየር ላይ ግጭት አደጋ በሕይወት የተረፈ ሰው እንዳልተገኘ ተገለጸ

ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ሮናልድ ሬገን አየር ማረፊያ አቅራቢያ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላንና አንድ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ተጋጭተው በደረሰው አደጋ አንድም በሕይወት የተረፈ ሰው እንዳልተገኘ ባለሥልጣናት ገለጹ።

የአሜሪካ አየር መንገድ ንብረት በኾነው የመንገደኞች አውሮፕላን ውስጥ 60 ተሳፋሪዎችና አራት የበረራ ሠራተኞች ተሳፍረው ነበር። በወታደራዊ ሄኪኮፕተሩ ደግሞ ሦስት ወታደሮች ነበሩ። ትላንት ሌሊት አደጋው ከደረሰበት ጀምሮ፣ የአስቸኳይ ጊዜ የርዳታ ሠራተኞችና የተለያዩ ኤጀንሲዎች በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት እጅግ ቀዝቃዛ በኾነው የፖተማክ ወንዝ ላይ ፍለጋ ቢያካሂዱም እስካኹን ማግኘት የቻሉት የ28 ሰዎችን አስክሬን ብቻ ነው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።