የዓለም መሪዎች የኦርላንዶውን ጅምላ ግድያ እያወገዙ ነው

  • VOA
    ሰሎሞን ክፍሌ

ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በኦርላንዶው ጥቃት ዙሪያ መግለጫ ሲሰጡ

በዩናይትድ ስቴትስ ፍሎሪዳ ክፍለ ግዛት ኦርላንዶ ከተማ በሀገሪቱ ታሪክ ከምንጊዜውም የከፋ በሆነው ጥቃት የመጪው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ታሳቢ ዕጩዎችን ጨምሮ ከዓለም ዙሪያም ጸሎትና የሐዘን መግለጫ እየተሰማ ነው።የዓለም መሪዎችም ድጊቱን አውግዘዋል።

ለሰለባዎቹ ጸሎት እንዲካሄድ፥ ቤተሰቦችንም ማጽናናት እንደሚያስፈልግ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንትነት በመወዳደር ላይ የሚገኙ እጩዎች አሳስበዋል።

የዲሞክራቲክ ፓርቲው ታሳቢ ዕጩ ሂላሪ ክሊንተን ለሲ.ኤን.ኤን ቴለቪዢን በሰጡት ቃል"ሀገራችንን በራሳቸው ተነሳሽነት ጥቃት ከሚያደርሱት መጠበቅ አለብን” ብለዋል። "ሁላችንም አሜሪካዊያን ሽብርተኝነትና ሌላም ሁከተኛ ተግባራትን አብረን እንደ አንድ አካል መታገል የምንችል መሆናችንን አጋጣሚው ያስገነዝበናል” ሲሉም አክለዋል።

የሪፐብሊካን ፓርቲው ተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትረምፕ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማና ሊሎች ዲሞክራቶች ሙስሊም የሆኑ ሽብርተኞችን ጽንፈኛ ብለው ለመጥራት ፈቃደኛ አይደሉም ብለው ለሚሰነዝሩት ውንጀላ ክሊንተን ምላሽ ሰጥተዋል። “እኔ ቃሉን መጥራት አልፈራም ፈቃደኛ የማልሆነው አንድን ሃይማኖት እንዳለ እንደጭራቅ ስሎ ጦርነት ማወጅን ነው” ብለዋል።

ባልደረቦቻችን Wayne Lee እና Smita Nordwall ያጠናቀሩት ዘገባ አለ።

ዝርዝርሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የዓለም መሪዎች የኦርላንዶውን የጅምላ ግድያ እያወገዙ ነው