የትረምፕና የኡን ፉከራዎች

North Korea Nuclear

North Korea Nuclear

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በሰሜን ኮሪያ ላይ የጀመሩትን የብርቱ ቃላት ድብደባ ዛሬ ይበልጥ አጠንክረው ቀጥለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በሰሜን ኮሪያ ላይ የጀመሩትን የብርቱ ቃላት ድብደባ ዛሬ ይበልጥ አጠንክረው ቀጥለዋል።

ፕዮንግያንግ የዩናይትድ ስቴትሷን የፓሲፊክ ውቅያኖስ ደሴት ጉአምን ለመደብደብ ያላትን ወታደራዊ ዕቅድ ከትናንት በስተያ ረቡዕ አሳውቃለች።

ሰሜን ኮሪያ ጉአም ላይ ጥቃት የመሠንዘር ውጥኗን ይፋ ያደረገችው በትንኮሣዋ የምትቀጥል ከሆነ ዓለም ቀድሞ አይቶት የማያውቅ የእሳትና የቁጣ ፍዳ ይወርድባታል ሱሉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከአሜሪካ ፕሬዚዳንት ተሰምቶ የማያውቅ የበረታ የዛቻ ውርጅብኝ ሳሙ ማግሥት ነው።

ፒዮንግያንግ በዩናይትድ ስቴትስ ግዛትም ሆነ ከወዳጆቿ በአንዱ ላይ እንዲህ ብላ ጥቃት ለማድረስ ብትሞክር “መዘዙ ከግምት በላይ ነው” ብለዋል ትረምፕ።

ይህ የሁለቱ መሪዎች የዛቻ ልውውጥና ጡንቻን የማገላበጥ አባዜ ሁለቱም ረገብ እንዲሉና አደብ እንዲገዙ የሚያሳስቡ ጥሪዎችና የግልግል ሃሣቦችን ጋብዟል።

ትረምፕ ለሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ያስተላለፍኩት መልዕክት ሊሆን ይገባው የነበረውን ያህል ጠንካራ አይደለም እያሉ ነው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የትረምፕና የኡን ፉከራዎች