እስራኤል በማዕከላዊ ቤይሩት የሄዝቦላህ ታጣቂዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት አደረሰች

  • ቪኦኤ ዜና

በሊባኖስ ቤይሩት የእስራኤል የአየር ጥቃት በደረሰበት ቦታ የነፍስ አድን ሰራተኞች በሥራ ላይ

Your browser doesn’t support HTML5

እስራኤል በማዕከላዊ ቤይሩት የሄዝቦላህ ታጣቂዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት አደረሰች

እስራኤል በሊባኖስ ዋና ከተማ በቤይሩት ማዕከላዊ አካባቢ ትላንት ሀሙስ በሂዝቦላህ ታጣቂዎች ላይ ባነጣጠረው ጥቃቷ ቢያንስ 22 ሰዎች ሲገደሉ 117 ሰዎች ቆስለዋል።

የባይደን አስተዳደር “እስራኤል በሄዝቦላህ ላይ የምታደርገውን ጥቃት እንደሚደግፍ፣ ሀገሪቱ ወደ “ሌላ ጋዛ” ስትለወጥ ማየት ግን እንደማይፈልግ” መናገሩን የቪኦኤ የዋይት ሀውስ ዋና ዘጋቢ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ ዘገባ አመልክቷል፡፡