Your browser doesn’t support HTML5
እስራኤል በኢራን ከሚደገፈው ሐማስ ጋራ የምታካሂደው ጦርነት፣ በሌባኖስ ወደሚገኘው ሄዝቦላ እና ወደ ኢራንም ሊስፋፋ እንደሚችል ፕሬዝደብት ጆ ባይደን ለወራት እስራኤልን ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል። እስራኤል በሌባኖስ ውስጥ ውጊያ በማድረግ ላይ መሆኗ እና ለቴህራን የሚሳኤል ጥቃትም ምላሽ እንደምትሰጥ መዛቷ፣ ብዙዎች የሚሰጉት ወቅት መምጣቱን የሚያሳይ ነው።
የቪኦኤ የዋይት ሃውስ ኃላፊ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ፣ የግጭቱን የመስፋፋት አቅምና አሜሪካ በቀጥታ ወደ ግጭቱ መግባት የመቻሏን ሁኔታ ተመልክታለች፡፡