ሦርያና ኢራቅ ውስጥ በሚገኘው “እስላማዊ ነውጠኛ ቡድኖች” ላይ ያነጣጠረ ዩናይትድ ስቴትስ መራሹ ጣምራ ጦር ዛሬ ሐሙስ እንዳስታወቀው፣ እአአ ከ2014 ወዲህ ብቻ 801 ሲቪሎች ተገድለዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ሦርያና ኢራቅ ውስጥ በሚገኘው “እስላማዊ ነውጠኛ ቡድኖች” ላይ ያነጣጠረ ዩናይትድ ስቴትስ መራሹ ጣምራ ጦር ዛሬ ሐሙስ እንዳስታወቀው፣ እአአ ከ2014 ወዲህ ብቻ 801 ሲቪሎች ተገድለዋል።
ይህ ዛሬ ይፋ የሆነው አኃዝ የተነገረው በወርኃዊው የጣምራ ቡድኑ መግለጫ ላይ ሲሆን፣ ባለፈው ጥቅምት ወር በወጡ 64 ሪፖርቶች 15 መሞታቸው ተመልክቷል። ሌሎች 695 ሪፖርቶች ደግሞ መረጃ ያልተገኘባቸው መሆናቸው ታውቋል።
“በሲቪሎች ላይ ሆን ተብለው ባልተፈጸሙ ግድያዎችና የመቁሰል አደጋዎች እኛ ኃላፊነት እንወስዳለን” ያለው መግለጫ፣ “ሁሉንም ሪፖርቶች ግን በትክክልና በተሟላ ሁናቴ ነው ከግምት የምናስገባው” ብሏል።