የጥር ስድስት መርማሪ ኮሚቴ ከቀድሞ የኋይት ሀውስ ረዳት የምስክርነት ቃል ተቀበለ

ካሲዲ ሀቺሰን

ካሲዲ ሀቺሰን

በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ላይ የተፈፀመውን ጥቃት የሚመረምረው የጥር ስድስት ኮሚቴ ከቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጽህፈት ቤት ሹም የማርክ ሜዶስ ረዳት የምስክርነት ቃል ተቀብሏል።

ካሲዲ ሀቺሰን የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እአአ የ2020 በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የተሸነፉበትን የምርጫ ውጤት ለመቀልበስ እየሞከሩ በነበረበት ወቅት በኋይት ሀውስ ቤተ መንግሥት ስለተደረጉ ውይይቶች ውስጥ አዋቂ ናቸው።

ኮሚቴው የካሲዲ ሀቺንግሰንን የምስክርነት ቃል እንደሚቀበል በሚስጥር ይዞ የቆየ ሲሆን ዛሬ ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ በፍጥነት የወሰነው ትናንትና መሆኑ ተገልጿል።

የጥር ስድስት መርማሪ ኮሚቴው "በቅርብ ያገኘውን ማስረጃ እናቀርባለን" ከማለት ውጭ ማንነታቸውን ይፋ ሳያደርግ ቆይቷል።