ኋይት ሐውስ ስለፕሬዝደንት ትረምፕ የጋዛ ዕቅድ ማብራራያ በመስጠት ላይ  ነው

  • ቪኦኤ ዜና

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ

Your browser doesn’t support HTML5

ኋይት ሐውስ ስለፕሬዝደንት ትረምፕ የጋዛ ዕቅድ ማብራራያ በመስጠት ላይ  ነው

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ጋዛን አልምተው "የመካከለኛው ምሥራቅ ሪቪየራ (የባሕር ዳር መዝናኛ)" ሲሉ ወደጠሩት ለመቀየር ላላቸው ሃሳብ ወታደሮችን የመላክ ዕቅድ እንደሌላቸው ኋይት ሐውስ ትላንት ረቡዕ አስታውቋል፡፡ ፍልጤማዊያኑ ወደ ሌላ ሀገር ሄደው አንዲሰፍሩ የሚደረገውም በጊዜያዊነት እንደሆነ ገልጿል፡፡

ይሕ ለውጥ የተደረገው ታዲያ ዕቅዱ በዓለም ዙሪያ ተቃውሞ ካስከተለ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም "ምንም ዓይነት የጎሣ ማጽዳት አድራጎት" እንዳይፈጸም ካስጠነቀቀ በኋላ ነው፡፡

የአሜሪካ ድምጽ የኋይት ሐውስ ዋና ዘጋቢ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ ያጠናቀረችው ዘገባ ነው።