በኢራን ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀቡ ከፍ ባለ መጠን ይጨመርባታል ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስታወቁ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ፕሬዚዳንቱ ይህ ያሉት የኒውክሌር መርኃ ግብሩዋን ለመገደብ የታለመውን ዓለም አቀፍ ሥምምነት በመጣስ ጭራሽ ኒውክሌርን እጅ መጠምዘዣ አድርጋ እየተጠቀመች ነው ስትል ዩናይትድ ስቴትስ ቴህራንን እየወነጀለች ባለችበት ባሁኑ ወቅት ነው፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ቪየና ላይ በተካሄደ የዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ድርጅት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ኢራን ኒውክሌር መርኃ ግብሩዋን የምታስፋፋው የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ እጅ ጠምዝዛ ገንዘብ ለመቀበል የምታደርገው ያገጠጠ ምክንያት ሌላ ሊሆን አይችልም ስትል ወንጅላለች።