አሜሪካ ነገ የነፃነት ቀኗን ታከብራለች

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

አሜሪካ ነገ የነፃነት ቀኗን ታከብራለች

የዩናይትድ ስቴትሷ ዋና መዲና ዋሽንግተን ዲሲ፣ ነገ ለሚከበረው የአገሪቱ 247ኛ ዓመት የነፃነት በዓል እየተዘጋጀች ናት፡፡ በዚኹ ክብረ በዓል፣ አንዳንድ አነስተኛ የአገሪቱ ከተሞች፣ በውስጣቸው ያሉ ልዩ ልዩ ማኅበረሰቦችን በአንድ ላይ በሚያሳትፉ የራሳቸው ልዩ ዘይቤዎች፣ በዓሉን ያከብራሉ።

አንድ የቨርጂኒያ ትንሽ ከተማም፣ ከዋናው ቀን ቀደም ብላ በዓሉን አክብራለች፡፡

የቪኦኤው ሳቂብ አል ኢስላም ወደ ከተማዋ ጎራ ብሎ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።