ዩናይትድ ስቴትስ በጋና ዜጎች ላይ የቪዛ ዕገዳ ጣለች

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል፡- የዩናይትድ ስቴትስ የሃገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ኃላፊ ክሪስቲን ኒልሰን

ፎቶ ፋይል፡- የዩናይትድ ስቴትስ የሃገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ኃላፊ ክሪስቲን ኒልሰን

ዩናይትድ ስቴትስ በጋና ዜጎች ላይ የቪዛ ዕገዳ መጣሏን ትላንት አስታወቀች።

ዩናይትድ ስቴትስ በጋና ዜጎች ላይ የቪዛ ዕገዳ መጣሏን ስታስታውቅ፣ ዕርምጃው - ዩናይትድ ስቴትስን ለመጎብኘት የሚፈልጉ የዚያች የምዕራብ አፍሪካይቱ ሃገር ዜጎችን ጉዳይ ይበልጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል ተብሏል።

የትረምፕ አስተዳደር ዕገዳውን ያፀናው ጋና ከዩናይትድ ስቴትስ እንዲወጡ የታዘዙ ዜጎቿን ወደ ሃገራቸው መመለስ አልቻለችም ሲል በመክሰስ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ የሃገር ውስጥ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ኃላፊዋ ክሪስቲን ኒልሰን ስለዚሁ ባወጡት መግለጫ ጋና በዓለምቀፉ ሕግ መሠረት ከአሜሪካ እንዲወጡ የታዘዙ ዜግቿን የመቀበል ኃላፊነቷን አልተወጣችም ብለዋል።