Your browser doesn’t support HTML5
የትረምፕ ላይ የግድያ ሙከራ የመሣሪያ ቁጥጥርን ጉዳይ ዳግም አነጋጋሪ አድርጓል
በቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ላይ የተደረገው የግድያ ሙከራ፣ በመሣሪያ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በተመለከተ “ማንቂያ ደወል” እንደኾነ፣ የአሜሪካ የጤና አጠባበቅ ዋና ኃላፊ ቪቬክ መርቲ ተናግረዋል።
በአሜሪካ በመሣሪያ የሚፈጸሙ ሁከቶች፣ “የሕዝብ ጤና ቀውስ ናቸው፤" ሲሉም ኃላፊው በቅርቡ አመልክተዋል።
በአሜሪካ፣ ከጦር መሣሪያ ይዞታ ጋራ በተገናኘ የተደቀነውን አደጋ በተመለከተ፣ በመፍትሔ አሰጣጥ ላይ አሁንም ልዩነት አለ።
በዚኽ ጉዳይ ላይ፣ ቬሮኒካ ባልዴራስ ኢግሌሴያስ የላከችውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።