በሜሪላንዱ ዴሞክራት ሴናተር ቤንጃሚን ካርዲን የቀረበውና S.Res.432 የተሰኘው የሰብዓዊ መብቶች ህግ በምክር ቤቱ የውጪ ጉዳዮች ኮሚቴ መፅደቁ ተገለፀ።
ዋሽንግተን —
እአአ ባለፈው ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በ114ኛው ኮንግሬስ ላይ የቀረበውና የጸደቀው ህግ፣ በኢትዮጵያ ሁሉን ያካተተ አስተዳደር እንዲኖርም ያበረታታል። የቴኔሲው ሬፓብሊካን ሴናተር ቦብ ኮርከር ህጉን በመደገፍ፣ ዋናውን የህጉን አቅራቢ ሴናተር ቤንጃሚን ካርዲንን፣ እንዲሁም ተባባሪ አቅርቢ ሴናተሮችን አመስግነዋቸዋል።
የS.Res.432 የሰብዓዊ መብት ማስከበሪያ ህግን ከሜሪላንዱ ሴናተር ቤንጃሚን ካርዲን ጋር በመተባበር ያቀረቡት፣ የዴልዌሩ ዲሞክራት ክሪስቶፈር ኮንስ፡የማሳቹሴትሱ ዲሞክራት ኤድዋርድ ማከርይ፡ የኒው-ጄርሲው ዲሞክራት ቦብ መንደዝ እንዲሁም የፍሎሪዳውን ሬፓብሊካን ሴናተር ሩብዮ ናቸው፣ የሴናተር ኮርከርን ምስጋና ያገኙት።
የቴኔሲው ሬፓብሊካን ሴናተርና የውጪ ግንኙነቱ ኰሚቴ ሊቀ-መንበር ሴናተር ቦብ ኮርከር ስለ ህጉ በሰጡት አስተያየት፣ ይህን ብለዋል።
“ይህ ውሳኔ፣ ከኢትዮጵያ ጋር ባለን የጋራ ግንኙነት ውስጥ ጠቃሚ ናቸው ለምንላቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ትኩረት የሚሰጥ ህግን ያካተተ ነው። ሁሉን ያካተተ የመልካም አስተዳደርና የሰብዓዊ መብት አያያዝ ማሻሻል የመሰሉ፡ ከኢትዮጵያ በኩል መሰራት ያለባቸው ገና ብዙ ጉዳዮች አሉ።”
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5