የደቡብ ሱዳን መንግስት የሰላም ድርድሩን እንዳያደናቅፍ አሜሪካና የአዉሮፓ ሕብረት አስጠነቀቁ

  • እስክንድር ፍሬው

Your browser doesn’t support HTML5

የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር


የደቡብ ሱዳን መንግስት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገዋል በሚል ያሰራቸዉን አራት የቀድሞ ባለስልጣናት እንዲፈታና እርቁን እንዲቀላቀሉ የአሜሪካና የአዉሮፓ ባለስልጣናት አሳሰቡ።

በደቡብ ሱዳን የአሜሪካ ልዩ ልዑክ አምባሳደር Donald Booth እና የአዉሮፓ ሕብረት የምስራቅ አፍሪቃ ልዩ ወኪል Alex Rondos ረቡዕ እለት አዲስ አበባ ዉስጥ በሰጡት የጋራ መግለጫ፣ የደቡብ ሱዳን መንግስት ታሳሪዎቹ የሰላም ድርድሩ አካል እንደማይሆኑ ማረጋገጫ ካልተሰጠዉ ተወካዮቹን እንደማይልክ መግለጹን ተናግረዋል።

ሁለቱ ባለስልጣናት ይህ ተቀባይነት እንደሌለዉና የደቡብ ሱዳን መንግስት ጭምር ሁሉም ወገኖች በኢጋድ በሚመራዉ ድርድር እንዲሳተፉ አሳስበዋል። በፓለቲካ ሂደቱ ላይ እንቅፋት በሚሆኑ ግለሰቦችም ላይ ዓለም አቀፋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል።