ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ፣ ለብዙ ጊዜ ሲጓተት የቆየውን ምርጫ በቀጣዩ ዓመት የማታካሂድ ከሆነ፣ በድምፅ አሰጣጡ ላይ ምንም ዓይነት ዓለምቀፍ ዕርዳታ እንደማታገኝ፣ የዩናይትድ ስቴትሷ ልዑክ ኒኪ ሄሊ አስታወቁ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ፣ ለብዙ ጊዜ ሲጓተት የቆየውን ምርጫ በቀጣዩ ዓመት የማታካሂድ ከሆነ፣ በድምፅ አሰጣጡ ላይ ምንም ዓይነት ዓለምቀፍ ዕርዳታ እንደማታገኝ፣ የዩናይትድ ስቴትሷ ልዑክ ኒኪ ሄሊ አስታወቁ።
ሄሊ ይህን ያስታወቁት፣ ከሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ጋር ዛሬ አርብ ከተገናኙ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው።
Your browser doesn’t support HTML5
“ምንም ያህል ቢዘገይ፣ ዓመቱ ማለቂያ ላይ ሳይሆን፣ ነፃና ሀቀኛ ምርጫ በቀጣዩ እአአ 2018 እንዲካሄድ እንፈልጋለን” ያሉት ሄሊ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላም፣ ምርጫው በ2018 እንደሚካሄድ እንዲያሳውቁ አሳስበዋል።
ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ ምርጫ ማካሄድ የነበረባት እአአ በ2016 ነበር። ዳሩ ግን ካቢላም፣ ምንም እንኳ የሥልጣን ጊዜያቸው ባለፈው ታኅሣሥ ወር ያበቃ ቢሆንም
“አልወርድም” አሉ፣ እናም ምርጫው ሳይካሄድ ቀረ።