ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ እያካሄዱ ያለው ለውጥ ከፍጥነትም ሆነ ከይዘት አንፃር የሚደነቅ መሆኑን ዩናይትድ ስቴትስ አስታውቃለች፡፡
አዲስ አበባ —
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ እያካሄዱ ያለው ለውጥ ከፍጥነትም ሆነ ከይዘት አንፃር የሚደነቅ መሆኑን ዩናይትድ ስቴትስ አስታውቃለች፡፡ ለእነዚህ የለውጥ ርምጃዎች መሳካት ሀገራቸው በአጋርነት መሥራት እንደምትፈልግም በኢትዮጵያ የአሜሪካ ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድም ከአንድ ሳምንት በኋላ ወደ ዋሺንግተን ያመራሉ፣ በዚያም ጉብኝት መልካሙን እንመኝላቸዋለን ያሉት ቃል አቀባዩ ኒኮላስ ባርኔት፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ጋር የሚደረግ ውይይት ሰለመኖሩ ግን አልጠቀሱም፡፡
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳምንታት በፊት በሰጠው መግለጫ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአሜሪካ ጉዞ ዓላማ፣ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር መወያየት ብቻ መሆኑን ጠቁሞ ነበር፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5