በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል ያሉ የልዩነት ጉዳዮችን “በፖለቲካ ውይይት መፍታት ያስፈልጋል” ሲሉ በአፍሪካ ቀንድ የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልዕክተኛ ተናገሩ፡፡
ልዩ መልዕክተኛው አምባሳደር ማይክ ሀመር፣ የፕሪቶሪያውን ስምምነት በተሟላ መልኩ መተግበር እንደሚያስፈልግ እና ሁለቱም አካላት ለዚህ ቁርጠኛ መሆናቸውን እንዳረጋገጡላቸው ገልጸዋል፡፡
በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ግጭቶችን በሠላም ለመፍታት ሀገራቸው ስለምታደርጋቸው ጥረቶችም አብራርተዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ከተከታዩ ቪዲዮ ይከተታሉ።