ኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለዜጎቹ የዝውውር ማስጠንቀቂያ አወጣ

  • ቪኦኤ ዜና
አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ

አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ መግለጫ ማቅረባቸውን ተከተሎ፣ አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፣ የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርብ እየተከታተለ እንደሆነ አስታወቀ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ መግለጫ ማቅረባቸውን ተከተሎ፣ አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፣ የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርብ እየተከታተለ እንደሆነ አስታወቀ።

ምንም እንኳ በአሁኑ ወቅት በሴኩሪቴው ጉዳይ ላይ የፈጠረው ተፅዕኖ በውል ባይታወቅም፣ በተጠባጩ የፖለቲካው ሁኔታ መሠረት፣ አንዳች ያልተፈለገ የፀጥታ ጉዳይ ሊከሰት እንደሚችል ያስታወሰው የኤምባሲው ማሳሰቢያ፣ ማንም የኤምባሲ ሠራተኛ በአሁኑ ወቅት ከአዲስ አበባ ውጪ ለመጓዝ፣ አስቀድሞ ኤምባሲውን ማሳወቅ ያስፈልጋል ብሏል።

አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ለማንኛውም፣ የሀገር ውስጥ መገናኛ አውታሮችን መከታተል፤ ባለሥልጣናት የሚሰጡትን መመሪያ በመከተል፣ ከተለያዩ ስብሰባዎችና ሕዝባዊ ሰልፎች መራቅ፣ አካባቢን በዐይነ ቁራኛ መቃኘት፣ የኢትዮጵያ የወቅታዊ ሁኔታ ያልተረጋጋ በመሆኑ፣ በማንኛውም ባልታሰበና ባልተጠበቀ ጊዜና ሰዓት መጥፎ ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል ልብ ማለት ያስፈልጋል ሲል አስታውቋል።