ለመጭው ምርጫ የመጨረሻ ሩጫ - ባሜሪካ

ለመጭው የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ተፎካካሪ ዕጩዎችን ለመወሰን የሚያስችል ድምፅ መናገሻዪቱን ዋሺንግተን ዲሲ ጨምሮ ወደ አሥር በሚሆኑ ግዛቶች ድምፅ ይሰጣል።

ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ከሪፐብሊካኑ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጋር ለመጋፈጥ የዴሞክራቲክ ፓርቲው ብቸኛ ተስፈኛ ጆ ባይደን ዛሬ የፓርቲያቸውን ውክልና ሊቆናጠጡ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በምርጫው ብዙ ቁጥር ያላቸው የኮንግረሱ ሁለቱም ምክር ቤቶች መቀመጫዎችም ለፉክክሩ የቀረቡ በመሆኑ ሌሎችም ዴሞክራቲክና ሪፐብሊካን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ተፎካካሪዎችም በግዛቶቹ ውስጥ ለድምፅ ቀርበዋል።

የዛሬው ዕጩዎችን የመለያ ቅድመ ምርጫ እየተካሄደ ያለው በኮቪድ 19 ምክንያት የተዘጉ ንግዶችና መሥሪያ ቤቶች ገና ሙሉ በሙሉ ባልተከፈቱበትና በጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ሞት ምክንያት ሃገሪቱ በሰልፎችና በሁከቶች በተጥለቀለቀችበት ሁኔታ ውስጥ ነው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ለመጭው ምርጫ የመጨረሻ ሩጫ - ባሜሪካ