ኒውዮርክ ከተማ ነገ ማክሰኞ ከሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዋዜማ የሁለቱን የዋና ዋና ፓርቲ ዕጩዎች ለማስተናገድ እየተሰናዳች ባለችበት በአሁኑ ወቅት የከተማይቱና የፖሊስ ባለስልጣናት የዕጩዎቹን ደህንነት ለማረጋገጥ በትጋት በመሥራት ላይ ናቸው፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ —
የማራቶን ሯጮችና አድናቂዎቻቸውን፤ እንዲሁም ለምርጫ ዘመቻ የተሰማሩትን የሁለቱን ዕጩዎች ደጋፊዎች ጨምሮ ሁሌም እንግዳ የማታጣና ድምቀት የማይለያት ከተማ ከመቼውም በላይ በሠው ጎርፍ ተጥለቅልቃለች።
ይህ ሁሉ ዓለምአቀፉ አሸባሪ ቡድን አልቃይዳ ጥቃት ሊሰነዝር ሊያቅድ ይችል ይሆናል የሚል የፀጥታ ጥንቃቄ አስፈላጊነት ወሬ እየተሰማ ባለበት ነው።
“ቢግ አፕል” በሚለው ዘመን የጠገበ የቁልምጫ ሥሟ የምትታወቀውን ከተማ ደማቅ ገጽታና ባለ ቀለም ድምፆች በተመለከተ የአሜሪካ ድምጿ ካሮሊን ፐርሱዩት ዘገባ አድርሳናለች።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5