ዩናይትድ ስቴትስ በተመድ ሰብአዊ ምክር ቤት አባልነት ተመረጠች

  • ቪኦኤ ዜና
The logo of the United Nations

The logo of the United Nations

የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ትናንት ሀሙስ ዩናይትድ ስቴትስን የድርጅቱ የሰአብዊ መብት ምክር ቤት አባል አድርጎ መርጧታል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ቀደም ሲል በትራምፕ አስተዳደር ዘመን ምክር ቤቱ ለእስራኤል ስር የሰደደ ተቃውሞ አለው በሚል 47 አባላት ካሉት ምክር ቤት ለሶስት ዓምታት ራሷን አግልላ ቆይታለች፡፡

ያለምንም ተቃውሞ ለእጩነት የቀረበችው ዩናይትድ ስቴትስ 193 አገሮች በሚስጥር በሰጡት ድምጽ 168 ድምጽ አግኝታለች፡፡

ዋሽንግተን፣ የምክር ቤት አባልነታቸው በዚህ ዓመት ጥር ላይ ከሚጀምረው የቻይናና ሞስኮ መንግሥታት ጋር ሊያጋጫት እንደሚችልም ይጠበቃል፡

ፕሬዚዳንት ባይደን ሥልጣን ከያዙበት ቀን ጀምሮ ፣ሰብአዊ መብት የውጭ ፖሊሲያቸው ማዕከል መሆኑን በመግለጽ እንደ ቻይናና ሩሲያ የመሳሰሉትን ሲተቹ ቆይተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ሮይተርስ እስካሁን ያለው የአስተዳደሩ ሪከርድ የሚያሳየው፣ ለብሄራዊ ደህንነት ቅድሚያ መስጠት በሚል ሰበብ፣ ሰብአዊ የሰብአዊ መብጥ የሚጥሱ የሌሎች አገሮች ጉዳይ ገሸሽ ይደረጋል ብሏል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ያገኘችው ድምጽ ዝቅተኛው ሲሆን፣ የበለጠችው 144 ድምጽ ያገኘችው ኤርትራን ብቻ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የምክር ቤቱ አባል ሆነው በድጋሚ ከተመረጡ አገራት መካከል ኤርትራና ሶማልያን ጨምሮ ካሜሩን ህንድ አርጀኒቲናና ሌሎች አገሮች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡