“ከፊሊፒንስ ጋራ ያለን  አጋርነት ከአስተዳደሮች መለዋወጥም የሚሻገር ነው" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር ተናገሩ

  • ቪኦኤ ዜና

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን እና የፊሊፒንስ የብሄራዊ መከላከያ ሚኒስትር ጊልቤርቶ ቴዎዶሮ በኪዞን ሲቲ፣ ፊሊፒንስ፣ እአአ ኅዳር 18/2024

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን፣ ቻይና በፊሊፒንስ ላይ የወሰደችውንና ‘አደገኛ’ ያሉትን ድርጊት አውግዘው፤ በአወዛጋቢው የደቡብ ቻይና ባህር የፊሊፒንስ ኃይሎች ጥቃት ቢደርስባቸው፤ ‘ዩናይትድ ስቴትስ ከሀገራቸው ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ያላትን ማኒላን ትከላከላለች’ ሲሉ ቀደም ሲል ያሰሙትን ማስጠንቀቂያ አጽንኦት ሰጥተው ደግመዋል።

አዲሱን የ500 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ እገዛ ጨምሮ፣ አገራቸው ለፊሊፒንስ የምትሰጠው ጠንካራ ወታደራዊ ድጋፍ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደርም ይቀጥል እንደሆን፤ በፊሊፒንሷ ፓላዋ ግዛት በሥራ ጉብኝት ላይ ባሉበት ወቅት የተጠየቁት ኦስቲን የሚቀጥለውን የአስተዳደር እርምጃ መገመት እንደማይችሉ ተናግረዋል። ሆኖም በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ጠንካራ ጥምረት በአገሮቹ ውስጥ የሚደረጉትን “የአስተዳደሮች መለዋወጥ ተሻግሮ ይቀጥላል" የሚለውን እምነታቸውን ገልጸዋል።