አምስት አባላት ያሉት አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ቡድን የወቅቱን የፖለቲካ ሁኔታ ለመከታተልና በሃገሪቱ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝና እና በዴሞክራሲ ላይ ያተኮረ ጉብኝት ለማድረግ ነገ ወደ ኢትዮጵያ ያመራል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
አምስት አባላት ያሉት አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ቡድን የወቅቱን የፖለቲካ ሁኔታ ለመከታተልና በሃገሪቱ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝና እና በዴሞክራሲ ላይ ያተኮረ ጉብኝት ለማድረግ ነገ ወደ ኢትዮጵያ ያመራል።
በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ የሚጠይቀውን /ኤችአር 128/ የተባለውን የዩናይትድ ስቴትስ ረቂቅ ሕግ ያቀረቡት ኮንግሬስማን ክሪስ ስሚዝ አንደኛው የልዑካኑ ቡድን አባል ናቸው።
የተወካዮቹ ምክር ቤት አባል ክሪስ ስሚዝ - በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያን መንግሥት ባለሥልጣናት ሲወተውቱ የቆዩት እአአ ከ2005 ዓ.ም በፊት ጀምሮ መሆኑ ይታወቃል።
አሁን ግን ይላሉ ኮንግሬስማን ስሚዝ አሁን ግን የወቅቱ መንግሥት የተስማማባቸውን ጠቃሚ ነጥቦች በግልፅ አስቀምጧል። የአፋን ኦሮሞ አገልግሎት ባልደረባ ሦራ ሓላኬ ነው ክሪስ ስሚዝን ያነጋገራቸው።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
Your browser doesn’t support HTML5
Your browser doesn’t support HTML5