የኮቪድ-19 ክትባት

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል

ፎቶ ፋይል

ኖቫቫክስ የተባለው የዩናይትድ ስቴትስ የክትባት ኩባኒያ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቱን ሁለተኛ ምዕራፍ የሰው ላይ ሙከራ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሊጀምር ነው።

የኮሮናቫይረስ ስርጭት እያሻቀበ ባለባት ሃገር በሚካሄደው ሙከራ ጤናማ የሆኑ 2665 አዋቂዎች የሚሳተፉበት እንደሚሆን ኩባኒያው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በተጨማሪም ኤችአይቪ በደማቸው ያለ ነገር ግን በደህና የጤና ሁኔታ ላይ ያሉ 240 ሰዎች ላይ ክትባቱ ምን ዓይነት ውጤት እንደሚያመጣም ይፈተሻል።

ኖቬቬክስ ከደቡብ አፍሪካ በተጨማሪ በቅርቡ ዩናይትድ ስቴትስ እና አውስትራሊያ ውስጥም ተመሳሳይ ሙከራዎች እንደሚያደራጅ ገልጿል።