በቻይና ለረጅም ዓመታት ታስረው የነበሩ ሦስት አሜሪካውያን ተለቀቁ

ሃሪሰን ሊ የአባቱን ካይ ሊ ፎቶ ይዞ

በቻይና ለረጅም ዓመታት ታስረው የነበሩ ሦስት አሜሪካውያን መለቀቃቸውን ዋይት ሃውስ አስታውቋል። የባይደን አስተዳደር በመጨረሻዎቹ የሥልጣን ዘመኑ ወራት ከቤጂንግ ጋራ የፈፀመው ዲፕሎማሲያዊ ስምምነት ነው ተብሏል።

የአሜሪካ መንግሥት ማርክ ስዊዳን፣ ካይ ሊ እና ጃን ሊዩንግ የተባሉት ሦስቱ አሜሪካዊያን ካለ አግባብ ተይዘው ቆይተው አሁን ወደአገራቸው ለመመለስ በቅተዋል ሲል አስታውቋል። ቻይና በበኩሏ እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን የምናስተናግደው በሕጉ መሠረት ነው ብላለች፡፡

ማርክ ስዊዳን ከአደንዛዥ ዕጽ ጋራ በተያያዘ በቀረበበት ክስ የሞት ቅጣት በመጠባበቅ ላይ የነበረ ሲሆን፣ ካይ ሊ እና ጃን ሊዩንግ ደግሞ በስለላ ተጠርጥረው ነበር የታሰሩት፡፡

በባይደን አስተዳደር የመጨረሻ ወራት ላይ ቤጂንግ ከአሜሪካ ጋራ የፈጸመችው ብዙም ያልተለመደ ዲፕሎማሲያዊ ስምምነት እንደሆነ ተነግሯል።

አሜሪካውያኑ ከ3 እስከ 12 ዓመታት በቻይና እስር ቤቶች ማሳለፋቸውም ታውቋል።