የትረምፕና የትዊተር ፀብ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የአሜሪካን ሕዝብ ሃሣብን የመግለፅ መብቶች “ከጥቃት ለመከላከል” በሚል በማኅበራዊ መገናኛ መረቦች ላይ ቁጥጥር የሚያሰፋ የአፈፃፀም ትዕዛዝ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት፤ ግንቦት 20/2012 ዓ.ም. ፈርመው አውጥተዋል።

ፕሬዚዳንቱን በእጅጉ ያስቆጣቸውና ወደ እንዲህ ዓይነት እርምጃ የወሰዳቸው በዚህ ሣምንት መጀመሪያ ላይ ባውጧቸው ሁለት መልዕክቶች ላይ ትዊተር የጭብጥ ወይም የመረጃ እውነትነት ማጣሪያ ማስጠንቀቂያ ማስቀመጡ ነው።

ትዊተር ትናንትናውኑ ባወጣው መግለጫ ይህ ትዕዛዝ “የሃገሪቱ መለያ የሆነውን መሪ ሕግ የሚጥስ ነው” ብሎታል። ትዊተር አክሎም “ይህንን ሕግ ለመሸርሸር በግላቸው ያደረጉት ጥረት የወደፊቱን ሃሣብን በኢንተርኔት የመግለፅ ነፃነትንና የኢንተርኔት ነፃነትንም አደጋ ላይ የሚጥል ነው” ብሏል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ትዕዛዛቸውን ከፈረሙ በኋላ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡ ጊዜ “በሕጋዊ መንገድ መዝጋት ቢቻል ኖሮ እዘጋው ነበር” ብለዋል ስለትዊተር ሲናገሩ።

የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን

በሌላ በኩል ደግሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ልዩ አማካሪ የሆኑት ዶሚኒክ ከሚንግስ “የኮቪድ-19 ታማሚ ሆነው ሳለ ከሰው ተነጥሎ የመቆየት መመሪያዎችን ጥሰዋል” በሚል የሃገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎችን ካወጡ በኋላ በመንግሥቱና በፕሬስ መካከል ያለው ግንኙነት በእጅጉ ሻክሯል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የትረምፕና የትዊተር ፀብ