የዩናይትድ ስቴትስ ዐቃቤ ሕግ ከቦይንግ ኩባንያ እና ተጎጂ ቤተሰቦች ጋራ እየተወያየ ነው

ፎቶ ፋይል፦ የቦይንግ አዲስ የተስፋፋው 737 ማቅረቢያ ማዕከል ሲያትል

በቦይንግ ኩባኒያ ላይ ሊቀርብ የሚችለውን ክስ ተከትሎ፣ የአሜሪካ ዐቃቤ ሕግ፥ ከኩባኒያው እና ከተጎጂ ቤተሰቦች ጋራ ውይይት እያካሔደ ነው፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ ዐቃቤ ሕግ ከቦይንግ ኩባንያ እና ተጎጂ ቤተሰቦች ጋራ እየተወያየ ነው

የዩናይትድ ስቴትስ ፍትሕ ሚኒስቴር፣ ቦይንግ ኩባንያ በወንጀል ይከሰስ እንደኾን ውሳኔ ለመስጠት ቀነ ገደብ ካስቀመጠበት ከሰኔ 30 ቀን በፊት፣ ዐቃቤ ሕጎች፥ ከኩባንያው እና በአውሮፕላኖቹ አደጋዎች ሕይወታቸው ካለፈ መንገደኞች ቤተሰቦች ጋራ እየተነጋገረ መኾኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በቦይንግ ኩባኒያው ላይ እየተሰነዘሩ ባሉት ክሶች እና በቀረበው የጥፋተኝነት ዕምነት ድርድር ጉዳይ ላይ በተለያዩ የዜና አውታሮች የተጠናቀሩ ዘገባዎችን ያካተተው ዝግጅት ዝርዝሩን ይዟል።