ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ የፀረ-ሽብር ሥልጠና መስጠት ጀመረች

  • ቪኦኤ ዜና

ዩናይትድ ስቴትስ ለአፍሪካ ወታደራዊ ኃይሎች በየዓመቱ የምታካሂደው የፀረ-ሽብር ሥልጠና /ፍሊንቶልክ/ ፕሮግራም ተካፋዮች በአይቮሪ ኮስት እአአ 20/2022

ዩናይትድ ስቴትስ ለአፍሪካ ወታደራዊ ኃይሎች በየዓመቱ የምታካሂደውን የፀረ-ሽብር ሥልጠና ፕሮግራም ትናንት በአይቮሪ ኮስት መስጠት ጀምራለች። ሥልጠናው የሚካሄደው እስላማዊ ታጣቂዎች በአፍሪካ በርካታ ቦታዎችን በተቆጣጠሩበት፣ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቶች በተበራከቱበት እና የፈረንሳይ ወታደሮች ያላቸውን ኃይል እየቀነሱ ባሉበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል።

ፍሊንቶልክ በመባል የሚታወቀው ይህ ዓመታዊ ሥልጠና ከምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡ 400 ወታደሮች የሚሰጥ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ አል-ቃይዳ እና እስላማዊ መንግሥት ከተባሉት ቡድኖች ጋር ግንኙነት ባላቸው አካላት በተደጋጋሚ ጥቃት ከሚደርስባቸው ሀገራት የተውጣጡ ናቸው።

ሆኖም የጊኒ እና እስላማዊ ጥቃት ያጠቃቸው የማሊ እና ቡርኪና ፋሶ ወታደሮች በሀገራቱ በተደረገው መፈንቅለ መንግሥት ምክንያት በሥልጠናው አልተካፈሉም።

እ.አ.አ ከ2013 ጀምሮ ፈረንሳይ በማሊ እስላማዊ ታጣቂዎቹን ስትዋጋ ብትቆይም፣ ጣልቃ ገብነቷን የሚቃወሙ ሰዎች ቁጥር እያደገ በመምጣቱ ባለፈው ሳምንት ከማሊ እንደምትወጣና ወደ ኒጀር ፊቷን እንደምታዞር ማስታወቋ ይታወሳል።