የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናጅ በኢትዮጵያ

  • እስክንድር ፍሬው

የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናጅ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ

በከፍተኛ የስብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ባለሥልጣናት ገንዘብ እንዲታደግ ከኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበ ጥያቄ ስለመኖሩ፣ አናረጋግጥም፣ አናስተባብልም ሲሉ አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን ተናገሩ፡፡

በከፍተኛ የስብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ባለሥልጣናት ገንዘብ እንዲታደግ ከኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበ ጥያቄ ስለመኖሩ፣ አናረጋግጥም አናስተባብልም ሲሉ አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን ተናገሩ፡፡

ስለጉዳዩ የተጠየቁት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናጅ፣ እንደዚህ ዓይነት ነገሮችን በአደባባይና በይፋ አንናገርም ነው ያሉት፡፡ ሀገራቸው በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ የማሻሻያ ዕርምጃዎችን እንደምትደግፍም፣ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

Your browser doesn’t support HTML5

የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናጅ በኢትዮጵያ