ዩናይትድ ስቴትስ ተጨማሪ ወታደራዊ ኃይል ከኢራቅ አስወጣች

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል

የዩይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል በያዝነው ወር፣ ተጨማሪ ወታደሮቹን ከኢራቅ ማስውጣቱን አስታውቋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ ሃላፉ ፍራንክ ምኬንዚ፣ ዛሬ ኢራቅን በጎበኙት ወቅት፣ በሃገሪቱ ያሉት የአሜርካ ወታደሮች፣ ከ 5,200 ወደ 3,000 እንደሚቀንሱ ገልጸዋል።

የወታደሮቹ ቁጥር መቀነስ፣ የኢራቅ አጋሮቻችን እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን ርዝራዦችን ከአካባቢው እንዲነቅሉ፣ በአማካሪነት ለመርዳት ያስችለናል ብለዋል ወታደራዊው ኃላፊ። የአሜሪካ ወታደሮቹ እንዲቀነሱ የተወሰነው፣ የኢራቅ የፀጥታ ኃይሎች ራሳቸውን ችለው የመስርት ብቃት እንዳላቸው ስለተረድን ነው ብለዋል።