የስደተኞችን ቀውስ ለማስወገድ ዓለምአቀፉ ህብረተሰብ ጠንካራ እርምጃ መውሰድ አለበት ሲሉ፥ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሳማንታ ፓወር ጥሪ አቀረቡ።
ዋሽንግተን —
አምባሳደሯ ትላንት ይህን ጥሪ ያቀረቡት፥ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ የሰላም ማዕከል ተገኝተው ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው። ዩናይትድ ስቴትስ በጠቅላላው ተቀብላ ለማስተናገድ ቃል ከገባችው 100,000 ሺህ ስደተኞች ውስጥ እአአ በ 2016 እና በ2017 ዓ.ም 30,000 ሺህ የሚሆኑትን ለመቀበል ጥረቷን የማጠናከር እቅድ እንዳላትም በዚሁ ንግግራቸው ላይ አስታውቀዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
‘የስደተኞችን ቀውስ ለማስወገድ ዓለምአቀፍ ህብረተሰብ እርምጃ መውሰድ አለበት’ በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር