የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ኃይል በሶማሊያ ስድሥት የአልሻባብ ታጣቂዎችን ገደለ

  • ቪኦኤ ዜና
የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ኃይል ዛሬ ረቡዕ ደቡባዊ ሶማሊያ ውስጥ ባካሄደው ጥቃት ስድሥት የአልሻባብ ታጣቂዎችን መግደሉ ተገለጠ።

የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ኃይል ዛሬ ረቡዕ ደቡባዊ ሶማሊያ ውስጥ ባካሄደው ጥቃት ስድሥት የአልሻባብ ታጣቂዎችን መግደሉ ተገለጠ።

የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኃይል የአፍሪካ ዕዝ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሆነ ጥቃቱ የተካሄደው ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ሁለት መቶ ስድሳ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ መሆኑን ገልጿል፣ ሌላ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

በሦስት ዒላማዎች ላይ የተነጣጠሩት የአየር ጥቃቶች የተካሄዱት ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር በተቀናጀ መንገድ መሆኑን መግለጫው አመልክቱዋል።

የዛሬው ጥቃት እኤአ ከሃምሌ አንድ ቀን ወዲህ የዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎች በሽብርተኛው አልሻባብ ላይ ያካሄደው አሥራ ሁለተኛ ጥቃት መሆኑን ዜናው አክሎ ገለጿል።

ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው ሳምንት በሰው አልባ አውሮፕላን ባካሄደቻቸው ሁለት ጥቃቶች አራት የአልሸባብ አባላትን መግደሏን አስታውቃለች፡፡

በተያያዘ ዜና የአልሸባብ ተዋጊዎች ኬንያ ድንበር ላይ በምትገኝ “በለድ ሃዎ” በተባለች ከተማ ባካሄዱት ጥቃት የሚበዙት የክልሉ መንግሥት ወታደሮች የሆኑ አሥራ ስድስት ሰዎች ገድለዋል።