ዩናይትድ ስቴትስ፣ የመንዋ ባይዳ ክፍለ ሀገር በሚገኙ ሁለት የ”እስልምና መንግሥት ነኝ” ባዩ ቡድን የማሰልጠኛ ካምፖች ባካሄደችው የአየር ጥቃት ብዛት ያላቸው የቡድኑ ተውጊዎች መግደሏን የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ገለጠ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ዩናይትድ ስቴትስ፣ የመንዋ ባይዳ ክፍለ ሀገር በሚገኙ ሁለት የ”እስልምና መንግሥት ነኝ” ባዩ ቡድን የማሰልጠኛ ካምፖች ባካሄደችው የአየር ጥቃት ብዛት ያላቸው የቡድኑ ተውጊዎች መግደሏን የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ገለጠ።
የመከላከያ ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ የመን የአሸባሪዎች ማሰልጠኛ ካምፖች መናሃሪያ ነች ብሏል ።
ሽብርተኛ ቡድኖች የመን ውስጥ ያለውን ብጥብጥና የአመራር ህዋ አጋጣሚውን ተጠቅመው ግዛቶችን ተቆጣጥረው እጅግ ደሃ በሆነችው ሃገር ያለባትን ችግር አባብሰውታል።
የመን ውስጥ የከፋ የምግብና የመድሃኒት እጥረት ከመኖሩም በላይ የኮሌራ ወረርሽኙ ሕዝቡን ለከፋ ስቃይ ዳርጎታል።