ዩኤስአይዲ በኢትዮጵያ የእናቶችና የሕፃናት ሞት የመቀነስ መርኃ ግብሩ

  • እስክንድር ፍሬው

የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክል ሬኖር

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምቀፍ የልማት ተራድዖ ድርጅት /ዩኤስአይዲ/ በኢትዮጵያ ያለውን የእናቶች እና የሕፃናት ሞት ለመቀነስ ያለሙ መርኃ ግብሮችን ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምቀፍ የልማት ተራድዖ ድርጅት /ዩኤስአይዲ/ በኢትዮጵያ ያለውን የእናቶች እና የሕፃናት ሞት ለመቀነስ ያለሙ መርኃ ግብሮችን ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡

አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክል ሬኖር ለአምስት አመት 1መቶ ሰማኒያ አንድ ሚሊዮን ዶላር የተመደበላቸው ፕሮጀክቶች ይፋ በተደረጉብት ሥነ ስርዓት ላይ ተገኝተዋል፡፡

በኢትዮጵያ አምባሳደርነታቸው የመጀመሪያ የሆነ ንግግርም አድርገዋል፡፡ ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ብቻ በየዓመቱ ሁለት መቶ ሚሊዮን ዶላር እየለገሰች መቀጠሏን አምባሳደሩ አስታውሰዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ዩኤስአይዲ በኢትዮጵያ የእናቶችና የሕፃናት ሞት የመቀነስ መርኃ ግብሩ