ዋሽንግተን ዲሲ —
የጂቡቲ የጸጥታ ሃይሎች ዛሬ በአንድ ሀይማኖታዊ ኩነት ላይ በከፈቱት ተኩስ በርካታ ሰዎች ሞተዋል ሲሉ እማኞች ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የሶማልኛ አገልግሎት ተናግረዋል።
የጸጥታ ሃይሎቹ ሃይማኖታዊው ኩነት እንዳይካሄድ ያስጠነቀቁ ቢሆንም አዘጋጆቹ ችላ እንዳሉትና ሟቹ ሃይማኖታዊ መሪ ሼኽ ዮኒስ ሙሴን ለማሰብ እንደተሰባሰቡ ምንጮች ጠቁመዋል።
የጸጥታ ሃይሎቹ የተሰባሰቡትን ሰዎች ለመበተን ሞክረው እንደነበር ጂቡቲ ያሉት ጋዜጠኞችና እማኞች ተናግረዋል። በሀገሪቱ ያለ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ቢያንስ ሁለት ሰዎች እንደተገድሉ ዘግቧል። ሌሎች ምንጮች ደግሞ ከዛ የበዛ ነው ይላሉ።
የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።
Your browser doesn’t support HTML5