የግጭት ተፈናቃዮችን ወደ ኦሮሚያ ክልል የመመለሱ ሥራ፣ ቅድመ ሁኔታዎች ባልተሟሉበት ሁኔታ መከናወኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል፡፡
ተጠልለው ከቆዩበት የአማራ ክልል ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዲመለሱ ከተደረጉ በኋላ ወደ ቀዬአቸው ለመግባት እንዳልቻሉ የገለጹ ተፈናቃዮች፣ “በቂ እና መሠረታዊ ድጋፍ ባለማግኘታቸው እንዲሁም የደኅንነት ስጋት ስላደረባቸው” ለመመለስ መገደዳቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ ወይም በምኅጻሩ ዩኤን-ኦቻ፣ ሒደቱ ቅድመ ኹኔታዎችን ካለማሟላቱ በተጨማሪ፣ ተመላሾቹ ደረጃቸውን ወዳልጠበቁ ጊዜያዊ ማቆያዎች እንደተወሰዱ አመልክቷል፡፡
መንግሥት በበኩሉ፣ “ተፈናቃዮቹ እንዳይመለሱ ይፈልጋሉ፤” ያላቸው አካላት ሒደቱን እያደናቀፉ እንደሆነ ገልጿል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።