በኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት ከ1000 በላይ ሰዎች በወባ ወረሽኝ ህይወታቸው ማለፉ ተገለጠ

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት ከ1000 በላይ ሰዎች በወባ ወረሽኝ ህይወታቸው ማለፉ ተገለጠ

ካለፈው አመት ጥር ወር አንስቶ በኢትዮጵያ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በወባ ወረርሽኝ ሳቢያ ለሕልፈት መዳረጋቸው እና ሌሎች ቁጥቸው 6 ሚሊዮን የሚደርሱ በወረርሽኙ መጠቃታቸውን፣ የመንግስታቱ ድርጅት የእርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ዩኤንኦቻ አስታወቀ።

ድርጅቱ ከትላንት በስቲያ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የተባለው አሃዝ ካለፈው ዓመት ጋራ ሲነፃፀር፣ የበሽታው ስርጭት መጨመሩን ማሳየቱን አመላክቷል፡፡ ይህንን አስመልክቶ አስተያየት እንዲሰጡ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ድሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት በአንዳንድ ተቋማት የሚወጡ ዘገባዎች፣ ለወረርሽኙ ተጋላጩን ሰው ቁጥር አስመልክቶ የሚሰጡ ግምቶች የሚያካትቱ በመሆናቸው አጠቃላይ አሃዙ ከፍ ሊል መቻሉን አመልክተዋል፡፡ ይህም ሆኖ በየሳምንቱ ቁጥሩ እስከ 2 መቶ ሺህ የሚደርስ ሕዝብ ለወባ ወረርሽኝ ተጋላጭ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለሕልፈት የሚዳገው ሰው ቁጥር ግን በሪፖርቱ ከተመለከተው አበአንጻሩ ያነሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡